inauguration

Inauguration
 

DC Agency Top Menu


-A +A
Bookmark and Share

ከመሄድዎ በፊት ይወቁ

ከመሄድዎ በፊት ይወቁ 

ከታች የሚገኘው መረጃ በምረቃው ሳምንት የሚካሄዱትን ጠቅላላ የሕዝብ ዝግጅቶችን ይመለከታል።

ተዘጋጁ 

 •  ረጃጅም ርቀቶችን በእግር ለመጓዝ ይዘጋጁ።
 • በፍተሻ ቦታዎች ረጃጅም መስመሮች  እንደሚኖር ይጠብቁ።
 • ከፍተኛ የህዝብ ብዛት ይኖራል - ትከሻ ለትከሻ ለመቆም ይዘጋጁ።
 • አብዛኛዎቹ የዝግጅቱ ተካፋዮች በመቆሚያ ክፍል አካባቢ ስለሚሆኑ ለረጅም ሰዓታት መቆም እንዳለባቸው ማወቅ አለባቸው። ህፃናትን፣ ወጣት ልጆችን፣ አዛውንቶችን ወይም የተዳከመ በሽታ የመከላከል አቅም ያላቸውን ለመውሰድ ሲታቀድ የበለጠ አሳቢነት መደረግ አለበት፡
 • መድሀኒት የሚወስዱ ሰዎች በጉብኝቱ ላይ ለሚቆዩበት ጊዜ በቂ መድሀኒት ማምጣት አለባቸው።  ጎብኚዎች ከሆቴሎቻቸው እና ከመቆያ ቦታቸው ለረጅም ሰዓቶች ስለሚርቁ፣ ማንኛውንም አስፈላጊ መድሀኒቶቻቸውን መያዝ አለባቸው።  በተጨማሪም ከቤታቸው ርቀው ሲሄዱ አደጋ ቢከሰት እና የጤና ሰነዶቻቸው ቢያስፈልጓቸው እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ከሀኪማቸው ጋር እንዲነጋገሩ ይበረታታሉ።
 • በቡድን የምትጓዙ ከሆነ፣ ከቡድናችሁ ዓባሎች ጋር ብትለያዩ የምትገናኙበት ቦታ አስቀድማችሁ ምረጡ።
 • የእጅ ስልካችሁን ባትሪ መሙላት እና ተጨማሪ የባትሪ መሙያ ይዛችሁ ለመምጣት አስቡ። ከከፍተኛ ጥሪ የተነሳ የእጅ ስልክ የሚሸፍነው የተወሰነ ቦታ ብቻ ሊሆን ስለሚችል አሳሳቢ የሆኑ መልዕክቶችን ለመላክ የቴክስት መልዕክት ተጠቀሙ።
 • የመታጠቢያ ቤቶችን፣ የመጀመሪያ ዕርዳታ የሚሰጥባቸውን ድንኳኖች እና ሙቀት የሚያገኙባቸውን ቦታዎች ይወቁ።
 • ለድንገተኛ ሁኔታ 911 ይደውሉ።

የዓየር ሁኔታ 

 • የዓየር ሁኔታ ትንበያ ከብሄራዊ የዓየር ሁኔታ አገልግሎት ይገኛል።
 • የበዓለ ሲመት እለት ብዙውን ጊዜ ቀዝቃዛ ነው - አብዛኛውን ጊዜ እኩለ ቀን ላይ 37°F እና አልፎ አልፎ እርጥብ ይሆናል።
  • በዋሽንግተን ዲሲ የበጋ ዓየር ሁኔታ  ሊለያይ ይችላል።  ከበድ ያለ አንድ ልብስ ከመልበስ ይልቅ በርካታ የተደራረቡ ሰፊ ልብሶች፣ ክብደት የሌላቸው፣ ሞቃታ ልብሶች መልበስ ይሻላል።
  • ቀዝቃዛ የዓየር ሁኔታ በልብ እና በሳንባዎች ላይ ተጨማሪ ጫና ይፈጥራል፣ ስለዚህ የልብ ህመም፣ ከፍተኛ የደም ግፊት ወይም የሳንባ ችግር ያለባቸው  ተሳታፊዎች ብርዱን እንዴት እንደሚቋቋሙ ከሀኪማቸው ጋር መነጋገር አለባቸው። 
  • የበረዶ ወይም የውሀ ክምችት ከተነበየ፣ ለዓየሩ ተስማሚ የሆኑ ጫማዎችን ማድረግ ያስቡ።

ደህንነት እና ፍተሻ 

 • በበዓለ ሲመት ሳምንት ተሳታፊዎች በማንኛውም የህዝብ ዝግጅት ከመግባታቸው በፊት ጥብቅ ፍተሻ ይደረግባቸዋል።  እባክዎ ተጨማሪ ሰዓት ይኑርዎት።
 • በበዓለ ሲመት ሳምንት በሚደረጉ የህዝብ ዝግጅቶች የሚከተሉት፣ ሊቀየሩ የሚችሉ፣ ነገሮችበዩኤስ ሲክረት ሰርቪስ የተከለከሉ ናቸው፤
 • የሚረጭ ጋዝ (ኢሮሶል)
 • ጥይቶች
 • እንስሳት፣ አገልግሎት ከሚሰጡ/ከሚመሩ እንስሳት በስተቀር
 • የሚታዘሉ ቦርሳዎች
 • ቦርሳዎች እና የልክ ገደቦችን የላቁ ምልክቶች
 • ቢስክሌቶች
 • ፊኛዎች 
 • ማቀዝቀዣዎች
 • ድሮኖች እና ሌሎች ያለሰው የሚበሩ የአውሮፕላን ሲስተሞች
 • ፈንጂዎች
 • የጦር መሣሪያዎች
 • የብርጭቆ፣ የሙቀት ወይም የብረት  መያዣዎች
 • ጨረር አመልካቾች
 • ኮረሪማ/በርበሬ መርጫ
 • ጥቅሎች
 • በካሜራ/ስልክ እራስን ማንሻ ዱላዎች
 • መዋቅሮች
 • የምልክቶች እና የማስታወቂያዎች ድጋፎች
 • የአሻንጉሊት ጠመንጃዎች
 • ፈንጂዎች
 • ማንኛውም ዓይነት መሳሪያዎች
 • ለደህንነት ጠንቅ ይሆናል የተባሉ ማንኛቸውም ነገሮች

አገልግሎት የሚሰጡ እንስሳት 

 • አገልግሎት የሚሰጡ እንስሳዎች በበዓለ ሲመት ዝግጅቶች ውስጥ ይፈቀዳሉ

የቦታማሳያአገልግሎቶችት ቦታዎች 

 • ተሳታፊዎች ሰዎችን የማግኛ አገልግሎቶችን እንዲጠቀሙ ለመርዳት የመገናኛ ድንኳኖች በናሽናል ሞል  አካባቢ ይኖራሉ። የዝግጅት ካርታውን ተመልሰው ይመልከቱ።